Skip to content

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 የወርቅ እና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎችን አሸነፈ

(ጅማ፣ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም) – በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ውድድር፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በወንዶች የቦርድ ቼዝ ጨዋታ 1 የወርቅ፣ እንዲሁም በሴቶች የቼዝ ጨዋታ 1 ወርቅ እና 1 የነሐስ በድምሩ 2 የወርቅ እና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎች አሸናፊ ሆኗል፡፡
በተመሳሳይ በወንዶች እና ሴቶች ጥንድ የቴኒስ ጨዋታ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኢንጂባራ ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 2 በማሸነፍ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ውስጥ ገብቷል፡፡
በሁለቱም ጾታዎች ለግል የበላይነት የሚካሄደው ውድድር በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ከአንድ እስከ ሦስት የሚወጡ ተወዳዳሪዎች ተሸላሚ ይሆናሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *