Skip to content

እንኳን ደስ አለን! 🥇🥇 🏆 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተጨማሪ 2 የወርቅ ሜዲሊያዎችን እና 1 ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል

ጅማ ፣ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም) – በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በፓራኦሎምፒክስ የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን እና የሻምፒዮና ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
ዩኒቨርሲቲው ይህንን ድል የተቀዳጀው በመስማት የተሳናቸው የወንዶች የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ሲሆን፣ በቡድን እና በጥንድ ጨዋታዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲን በመርታት ነው።
በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት የ1,500፣ የ5,000 እና የ100 ሜትሮች የማጣሪያ ውድድሮችን አድርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *