Category: Latest KUE-News

በዩኒቨርሲቲው የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ በተደረገው ውይይት፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በመክፈቻ ንግግራቸው የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ በተቀናጀ ቡድናዊ ሥራ (team work ) የተመዘገበ የጋራ ውጤት ነው ፤ በመሆኑም ለቀጣይ የተሻለ ሥራ የዚህኛውን ሴኬት፣ ተግዳሮት እና እንዲሁም ለተሻለ አፈፃፀም በተወሰዱት አማራጭ መፍትሔዎችን በደንብ መገምገም ቀጣይ […]

Read More

ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፣ ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ፡፡ ቢሮው ለከተማው ነዋሪዎች የተሻለ አገልግሎትን ለመስጠት እንዲችል ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በስልጠና፣ በጥናትና ምርምር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ አብሮ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባደረገው የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተሻለ አፈጻጸም በማሳየቱ […]

Read More
KUE football team

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድን 2-1 በሆነ ውጤት አሸነፈ

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ በመተሳተፍ ላይ የሚገኘው የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድን፣ ዛሬ ባደረገው ጨዋታ ተጋጣሚውን የኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ቡድንን 2-1 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡ ቡድኑን አሸናፊ ያደረጉትን 2 ጎሎችም የቡድኑ አጥቂ አሚር ሲራጅ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ አስመዝግቧል፡፡ ትናንት ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታው 1 አቻ የተለያየው የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 4 ነጥቦችን […]

Read More

“የቋንቋ መምህራን ተማሪዎች ቋንቋውን በፍላጎት እና በፍቅር እንዲማሩ እና እንዲለምዱ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትብብር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ ቋንቋዎችን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራን የሥራ ላይ ሥልጠና ተሠጠ፡፡ በስልጠናው መክፈቻ የቋንቋ መምህራን ተማሪዎቻቸው ያሉበትን ደረጃ ጠንቅቀው በመረዳት ከመሠረታዊው የቋንቋ ክሂሎት በተጓዳኝ ቋንቋውን በፍላጎት እና በፍቅር እንዲማሩ፣ እንዲለምዱ እና እንዲናገሩ ማስቻል ለዚህም የቋንቋ […]

Read More

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ በመሳተፍ ላይ ነው።

የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ጥር 17 ቀን 2017 በአዘጋጁ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረ ሲሆን፣ በመክፈቻ ሥነስርዓቱም ላይ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በርካታ ታዳሚዎች ተገኝተዋል። 49 ዩኒቨርሲቲዎችና ከ2500 በላይ ስፖርተኛ ተማሪዎች የሚሳተፉበት ውድድሩ በአምስት ዘርፎች ማለትም በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በባህል ስፖርት፣ በቼዝ […]

Read More

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በትምህርት ጥራት እና በምርምር መስኮች በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና በአፋር ትምህርት ቢሮ . መካከል ዛሬ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም የተፈረመው ስምምነት፣ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማብቃት ሞዴል የትምህርት ተቋም ለማድረግ የሚያስችሉ የሥልጠና እና የምርምር ሥራዎችን በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፣ በሀገራችን የትምህርት መስክ ዘመናትን […]

Read More

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሩ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሚከናወኑ ቁልፍ ተግባር አመልካቾች ርክክብ አደረጉ።

የኢ.ፊ.ዴ.ሪ ትምርህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢዎች እና ፕሬዚዳንቶች ጋር በየተልዕኮአችን ለ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም KPI: Performance Contract Agreement” መፈራረሙ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መነሻነትም ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በዩኒቨርስቲ ደረጃ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ከጽ/ቤት ሃላፊ ጋር በየዘርፎቻቸው ካስኬድ በተደረጉ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ላይ “Performance Contract Agreement” ተፈራርመዋል፡፡ በፊርማ […]

Read More

መምህራን ጊዜውን በሚመጥን ክህሎት፣ ዕውቀትና አመለካከት የታነፁ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የመማር ማስተማር ሂደትን ፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎትን በተመለከተ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር በ04/03/2017 ዓ.ም በተደረገው ውይይት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፈቀደ ቱሊ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሐሳብ፣ በዓለምዓቀፍ ደረጃ የሚታየው ለውጥ ፈጣን በመሆኑ መምህራን ጊዜውን የሚመጥን ክህሎት፣ ዕውቀትና አመለካከት እንዲኖራቸው ራሳቸውን በየጊዜው ማዘጋጀት እንዳለባቸው ገለጸዋል፡፡ለውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደት መምህራን ሁልጊዜም ማንበብና ምርምር […]

Read More

በ2017 ዓ.ም ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ

በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ አልፋችሁ ለ2017 የትምህርት ዘመን ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ህዳር 04 – 05 ቀን 2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

Read More

በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና PGDT በኤክስቴንሽን እንዲሁም በዶክትሬት ዲግሪ ለመማር ላመለከታችሁ

በ 2017 ዓ.ም ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሰቲ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና PGDT በኤክስቴንሽን እንዲሁም በዶክትሬት ዲግሪ ለመማር አመልክታችሁና ያለፋችሁ አመልካቶች ምዝገባ የሚከናወነው ከህዳር 13 – 15 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን …

Read More