KUE-Stakeholders Symposium: Strengthening Partnership for Quality Education in Ethiopia

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ “KUE-Stakeholders Symposium: Strengthening Partnership for Quality Education in Ethiopia” በሚል ርዕስ በትምህርት ጥራት ዙሪያ የተዘጋጀው ሲፖዚየም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እና በትብብር መሥራት የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል ወሳኝ እንደሆነ የሚያምነው ዩኒቨርሲቲው፣ በርካታ ተግባራትን በማከናውን ላይ ሲሆን፣ በዛሬውም መድረክ ላይ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴን ጨምሮ፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የትምህርት ኤክስፐርቶች፣ የመስኩ ዕውቅ ምሁራን እና ዓለምአቀፍ ተቋማት በተወያዪነት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *