የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ2016 ዓ.ም ያስፈተናቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉንም (100%) በከፍተኛ ውጤት ማሳለፍ መቻላችንን ስናበስር እጅግ ደስ እያለን ነው።
የተመዘገበው ውጤት ተማሪዎችን ከታች ይዞ መኮትኮት ከተቻለ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው።
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በአዲስ አበባ ከተማ ከ8ኛ ክፍል ወደ 9ኛ የሚሸጋገሩ ተማሪዎችን በመቀበል በዩኒቨርስቲው የበላይ አመራር ልዩ ክትትልና ድጋፍ ፤ ለዚሁ ተልዕኮ በተመረጡ መምህራን ማስተማር ከጀመረ ጀምሮ ለተከታታይ 5 ዓመታት (5ዙር) ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% ሲያሳልፍ የቆየ ሲሆን በዘንድሮው 100% በማሳለፍ እንደሀገር ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል ።
ከእነዚህ ውስጥ ፦
  • ከ600
  • 500 በላይ ያመጡ… 62.3%
  • 405- 499 ያመጡ … 37.7 %
  • በጣም ከፍተኛው… 553
  • ዝቅተኛው ( 405 )
ውጤቱ ቤተሰብን ፣ የትምህርት ቢሮን እና በአጠቃላይ የትምህርቱን ማህበረሰብ ያኮራ ውጤት ነውና ለዚህ ውጤት መምጣት ሌት ተቀን የለፋችሁ የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራንና ሠራተኞች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም የተማሪዎች ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ ።
✔️ ከሁሉ በላይ ውድ የነገ የሀገራችን ተስፋ የሆናችሁ ተማሪዎቻችን ባስመዘገባችሁት ውጤት ኮርተንባችኃል።
እንኳን ደስ አላችሁ።
ብርሃነመስቀል ጠና ( ዶ/ር )
የኮትዩ ፕሬዚዳንት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *