ለክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን የኢ-ለርኒንግ ገለፃ ተሰጠ

(ኮትዩ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም) – ገለፃውን ያስጀመሩት የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ ሙሉጌታ፣ ቴክኖሎጂ ከምንጊዜውም በፈጠነ ሁኔታ እየተስፋፋ በመሆኑ የክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም በቤታቸውም ሆነ በማንኛውም ሥፍራ ሆነው በኢ-ለርኒንግ ትምህርታቸውን መማርና በትምህርታቸውም ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተው መከታተል እና በተግባር ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የኢ-ለርኒንግ ማኔጅመት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ደረሰ ተርፋ እንደገለፁት፣ ለክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን የተሰጠው የኢ-ለርኒንግ ገለፃ ሰልጣኖቹ ትምህርታቸውን በኦንላይን እንዴት መማር እንደሚችሉ አስፈላጊውን ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው፡፡

ገለፃው የኢ-ሼ (e-SHE) ፕላትፎርምን በመጠቀም የክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን የኤስ ኤስ (SS) ኮርስን በመውሰድ እንዴት ውጤታማ እንደሚሆኑ፣ በክፍል ውስጥ ከተወሰነው የገፅ ለገፅ ትምህርት ባሻገር በየትኛውም ሥፍራ ሆነው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ፣ የተሰጣቸውን አሳይመንት በቀላሉ እንዲሰሩና እንዲልኩ፣ ተሳትፏቸው እንዲጨምርና በአጭር ጊዜ ውስጥ ግብረመልስ እንዲያገኙ የሚያስችል በመሆኑም ጠቀሜታው የላቀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ዓለም ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እየተሸጋገረ ነው ያሉት ዶ/ር ደረሰ ኢ-ለርኒንግ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኤሌክትሮኒክስ አማካኝነት በኦንላይን የሚካሄደውን የመማር ማስተማር ሂደት አሳታፊና ተደራሽ እንዲሁም ከተቀረው ዓለም ጋር ተወዳዳሪ የሚያደርግ ሲሆን ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት በዩኒቨርሲቲው የተሰጠው ገለፃም የተቋማዊ ኢ-ሜይል እና ሌሎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀሞችን ያካተተ ስለመሆኑም አመልክተዋል፡፡

በተሰጠው የኢ-ለርኒንግ ገለፃ ላይ ወደ 800 የሚጠጉ የክረምት ትምህርት ሰልጣኝ መምህራን የተሳተፉ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

– የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education

ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችችንን ይከታተሉ:

Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et

Website: https://www.kue.edu.et/

YouTube: https://youtube.com/@kueducation

Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *